Welcome to HiTEC Trading House

Leader in  Agricultural, Industrial and Building Technology

HiTEC Trading House

Call now

+251 911200226

Book a meeting

Welcome to HiTEC Trading House

Leader in  Agricultural, Industrial and Building Technology

የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን የሚያስተዋወቅና የባለሙያዎችን አቅም የሚያጎለብት የስልጠና መድረክ ተካሄደ። 


በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የመልካሣ ግብርና ምርምር ማዕከል የግብርና ምህንድስና ምርምር ዘርፍ ከሚያከናውናቸው የምርምር ስራዎች መካከል በምርምር የወጡና ከዉጭ የገቡ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ከአራት ክልሎች ለተመረጡ ባለ ድርሻ አካላት ማስተዋወቅ፣ የአጠቃቀምና አያያዝ ስልጠና መስጠትና፣ አርሶአደሮችን ከ ቴክኖሎጂ አምራቾችና አስመጪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር የሚያስችላቸው መድረክ በምርምር ማዕከሉ አካሂዷል። 


በመድረኩ ላይ ከአራት ክልሎች የተወጣጡ አርሶአደሮች፣ የሜካናይዜሽን ባለሙያዎች፣ የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የትራክተር አስመጪዎችና የሜካናይዜሽን መሣሪያዎች አምራቾች የተሳተፉ ሲሆን ድርጅታችን ሐይቴክ ትሬዲንግም በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ምርትና አገልግሎቱን አስተዋዉቋል። የድርጅታችን የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ኃላፊ የሆኑት አቶ. አህመድ መሐመድ ሐይቴክ ስለሚያቀርባቸዉ አነስተኛ የፈረስ ጉልበት ያላቸዉ ትራክተሮች እና መሣሪያዎች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፍላጎት ያላቸዉ አርሶአደሮችም ከድርጅታችን ጋር አብሮ ለመስራት እንዲበረታቱ በማሰብ ከአጋር የፋይናንስ ተቋማት ለማሽን ግዢ የሚዉል ብድር እንዳመቻቸም ለተሳታፊዎች አስረድተዋል።

Read More Articles

For inquiries, orders, or any other information, please reach out to us using the following contact details:

- Phone: +251 911200226 / +251116621198 / +251935998115

 - WhatsApp: +251 911200226

 - Email: info@hitecet.com

For inquiries, orders, or any other information, please reach out to us using the following contact details: